እኛው ነን ማገሮች!!

7 mins read
1

ወገን ግድግዳ ሁን፤ የዘመመ ቤታችንን ልናቀና ማገር ይዘን መጥተናል!

በፖለቲካ ፓርቲ ወይም በድጋፍ ሰጪ ድርጅት፣ በማኅበረሰብ፣ በልማት፣ በተራድኦ፣ ወይም በሌሎች አይነት ማኅበራትና ድርጅቶች በንቃት መሳተፍ፣ ወገናችንን ከጥፋት ለመታደግና የአገሩ ባለቤት እንዲሆን ለማስቻል ከምንከተላቸው የትብብር አማራጮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ሆኖም በየትኛውም የአደረጃጀት ዘርፍ ተሳትፈን የአማራውን ንቅናቄ የህልውናውን ዋስትና በሚያረጋግጥበት ጎዳና ለመምራት አላማችን አንድ መሆን አለበት። የአላማ አንድነት ማለት በአንድ መደራጀት አይደለም፤ በሃሳብ መገናኘት እንጂ።

ይህ ሁሉ ንቃትና መነሳሳት እንዲሁም ያልተቆጠበ ድጋፍ ባለበት፣ የአማራው ንቅናቄ በሚፈለገው ፍጥነት መራመድ ያቃተው ለምንድነው ብለን ስንጠይቅ፣ በሁሉም ዘርፍ ገዢ ሃሳቦችን ማፍለቅ፣ እንዲሁም በድርጅቶችና በማኅበራት፣ በጠቅላላውም በአማራው ህዝብና በሊቃውንቱ መካከል የሃሳብ ግንኙነት መፍጠር ባለመቻላችን እንደሆነ አስተውለናል፤ ገምግመናል።

ይህ አስተውሎት ከተቸከልንበት መንጥቆ ትልቅ እርምጃ እንድንራመድ አስችሎናል። የወገናችንን ህልውናና ክብር ለማስጠበቅ የሚያስፈልገው የአመራርና የእውቀት ድጋፍ አእምሯዊና ቁሳዊ አቅም ያላቸውን ልጆቹን በማስተባበርና ጠንካራ የመገናኛ ድርጅት በማቆም እንደሚገኝ በማመን እነሆ “እኛው ነን!” በሚል መሪ ቃል ማገር መገናኛን መሥርተናል።

በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም በያለንበት ሆነን በሃሳብና በአላማ ለመቀራረብ፣ ስለአገራችን ችግሮች በጋራ መክረን የሚበጀንን ለመምረጥ መገናኛችን ማገር ነው።

ታሪክ መርምረው፣ ሃሳብ አንጥረው መላ የሚፈጥሩ፣ የእውነትን መንገድ የሚያበሩና የሚመሩ ሊቆቻችንን፤ ግዙፍ አርቅቀው ረቂቅ አግዝፈው የሚያሳዩ ምናባውያን ጠቢቦቻችንን ይዘንና በዘመናዊ የመገናኛ መሳሪያዎች ታግዘን ህዝባችንን በሃሳብ በማገናኘት የወደፊት እድሉን የሚቆጣጠርበትን ማማ የምናቆምለት እኛው ነን!

1 Comment

  1. ግሩም ምናብ እና መነቃቃት። ወቅታዊ ጅማሮና ቁርጠኝነት የሚንፀባረቅ በት በግሩም እና ለዛ ባለዉ ቋንቋ የተዘጋጀ ሀተ ታ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ማገር እለታዊ ዜና 04/20/2022

በወለጋ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች የድረሱልን ጥሪ፣በራያ ቆቦ አዲስ የጸጥታ መመሪያ ተላለፈ፣ሱዳን አልፋሽጋ ግዛቴ ነዉ እወቁልኝ አለች

ማገር እለታዊ ዜና 04/19/2022

በወለንጭቲ ከባድ ተኩስ ተከፍቷልየሸዋሮቢቱ ጥቃት ሰለባዎችየሩሲያ ኢምባሲ ማስተባበያኮሎኔል ደመቀ ምን አሉ?