እኛው ነን ማገሮች!!

7 mins read

ወገን ግድግዳ ሁን፤ የዘመመ ቤታችንን ልናቀና ማገር ይዘን መጥተናል!

በፖለቲካ ፓርቲ ወይም በድጋፍ ሰጪ ድርጅት፣ በማኅበረሰብ፣ በልማት፣ በተራድኦ፣ ወይም በሌሎች አይነት ማኅበራትና ድርጅቶች በንቃት መሳተፍ፣ ወገናችንን ከጥፋት ለመታደግና የአገሩ ባለቤት እንዲሆን ለማስቻል ከምንከተላቸው የትብብር አማራጮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ሆኖም በየትኛውም የአደረጃጀት ዘርፍ ተሳትፈን የአማራውን ንቅናቄ የህልውናውን ዋስትና በሚያረጋግጥበት ጎዳና ለመምራት አላማችን አንድ መሆን አለበት። የአላማ አንድነት ማለት በአንድ መደራጀት አይደለም፤ በሃሳብ መገናኘት እንጂ።

ይህ ሁሉ ንቃትና መነሳሳት እንዲሁም ያልተቆጠበ ድጋፍ ባለበት፣ የአማራው ንቅናቄ በሚፈለገው ፍጥነት መራመድ ያቃተው ለምንድነው ብለን ስንጠይቅ፣ በሁሉም ዘርፍ ገዢ ሃሳቦችን ማፍለቅ፣ እንዲሁም በድርጅቶችና በማኅበራት፣ በጠቅላላውም በአማራው ህዝብና በሊቃውንቱ መካከል የሃሳብ ግንኙነት መፍጠር ባለመቻላችን እንደሆነ አስተውለናል፤ ገምግመናል።

ይህ አስተውሎት ከተቸከልንበት መንጥቆ ትልቅ እርምጃ እንድንራመድ አስችሎናል። የወገናችንን ህልውናና ክብር ለማስጠበቅ የሚያስፈልገው የአመራርና የእውቀት ድጋፍ አእምሯዊና ቁሳዊ አቅም ያላቸውን ልጆቹን በማስተባበርና ጠንካራ የመገናኛ ድርጅት በማቆም እንደሚገኝ በማመን እነሆ “እኛው ነን!” በሚል መሪ ቃል ማገር መገናኛን መሥርተናል።

በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም በያለንበት ሆነን በሃሳብና በአላማ ለመቀራረብ፣ ስለአገራችን ችግሮች በጋራ መክረን የሚበጀንን ለመምረጥ መገናኛችን ማገር ነው።

ታሪክ መርምረው፣ ሃሳብ አንጥረው መላ የሚፈጥሩ፣ የእውነትን መንገድ የሚያበሩና የሚመሩ ሊቆቻችንን፤ ግዙፍ አርቅቀው ረቂቅ አግዝፈው የሚያሳዩ ምናባውያን ጠቢቦቻችንን ይዘንና በዘመናዊ የመገናኛ መሳሪያዎች ታግዘን ህዝባችንን በሃሳብ በማገናኘት የወደፊት እድሉን የሚቆጣጠርበትን ማማ የምናቆምለት እኛው ነን!

Latest from Blog

“ከለቅሶው ድንኳን እንውጣ!”

ቋሚ ስለሟች የሚያለቅሰው ለራሱ ነው። ለቅሶ ሙትን እንደማይመልስ እያወቅን የምናለቅሰው፣ እጦታችን የፈጠረብንን ስሜት ልናበርድ ነው። ሞቱ