ጌታቸው በየነ በዛሬው የማገር እንግዳ ዝግጅቱ ከህግ ባለሙያው አቶ አሳምን መኮነን ጋር ህግ ነክ በሆኑ አገራዊ ርዕሰ ጉዳዯች ላይ ተወያይቷል:: በውይይቱ የሚነሱ ነጥቦች: • አገር በነገድ እና በጎሳ ተሸንሽና የታጠቀ ኃይል ሁሉ ንፁሃንን እያገተ እና እየገደለ ‘ፖለቲካ’ በሚሰራባት ኢትዮጵያ ‘አገራዊ ምክክር’ ምን ፋይዳ ይኖረዋል ? • ኢትዮጵያ ያለችበት ችግር አሁን በሚሄድበት ‘አገራዊ ምክክር’ በሚባለው መንገድ የሚቀረፍ ነው? • ህገ መንግስቱ አሁን በስልጣን ላይ ላለው ኃይል ትልቁ የኃይል እና ስልጣን ምንጭ መሆኑ ግልፅ ነው ይሁን’ና መንግስት ፍላጎቱ ቢኖረው ትልቁን የህገ መንግስት ቋጠሮ ለመፍታት ያለው አማራጭ ምንድን ነው?
መልካም ቆይታ!
ማገር ዝግጅት ክፍል