የአማራ ህዝብ ያለበትን የኅልውና ስጋት በማገናዘብ ኅልውናውን ለማስከበር መወሰድ ስለሚገባቸው ቆራጥ እርምጃዎች ከዓለም አቀፍ የአማራ ማኅበራት የተሰጠ መግለጫ።

39 mins read

ሚያዚያ 20 ቀን 2014 ( አፕሪል 29 2022)|

በቃን! የመጨረሻው ሞገድ
በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአማራ ማኅበራት መሪዎች በፋና (የአማራ ማኅበራት ህብረት በሰሜን አሜሪካ) እና በካሳ ( በካናዳ የአማራ ማኅበራት ህብረት) አስተባባሪነት፣ ከጥር 13 እስከ ጥር 15፣ 2014 ዓምበአትላንታ ከተማ ‘ለአማራ የህልውና ትግል የእኛ ተግባራዊ ምላሽ ምን ይሁን?’ በሚል መሪ ጥያቄ 3ኛ የአማራ ድርጅት መሪዎች ጉባኤ አካሂደን፤ በአሁኑ ግዜ የሚታየውን አማራ ህዝብ ላይ የተደቀነውን አደጋ ቀድሞ ያመላከተ የአቋም መግለጫ አውጥተን ነበር። በግዜውም ከሌሎች በጣም ወሳኝ ከሆኑ አቋሞች መሃከል በስር ነቀል ለውጥ ኢሕአዴግን ለመጣል ተቀጣጥሎ የነበረው ትግል ለግዜው ብልጭ ብሎ በጠፋው የለውጥ ቃል ኪዳን እንደተዳፈነ አስታውሰን፤ የለውጡ ቃል ኪዳን ፈጽሞ እንደታጠፈ ገልፀን በ2010 ዓም (2018 GC) የተቋረጠው የስር ነቀል ለውጥ ትግል እንዲቀጥል አቋም መያዛችን ይታወሳል።

በአቋም መግለጫው እንደታለመው ይህ ስብስብ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ በመላው አለም ከሚገኙ የአማራ እንቅስቃሴ ድርጅቶች ጋር በተለያዩ ወሳኝ ጉዳዮች ሲመክር የሰነበተ ሲሆን፤ እንደ አዲስ የተጀመረውን ትግል በሁሉም የባለድርሻ አካላት እኩል ለማስኬድ የተለያዩ የንግግር መድረኮችን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። በሌላ በኩል፤ በሕዝባችን ላይ በየአቅጣጫው የሚሰነዘረው የጥቃት ዘመቻ በአይነትም፤ በብዛትም በጣም እየጨመረ መምጣቱን ሰሞኑን ካየናቸው ክስተቶች ተገንዝበናል። ከብዙዎቹ በጥቂቱ ለመጥቀስ፡

ሀ) የምዕራባውያን መንግስታት እና ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የተቀናጀ በሚመስል አካሄድ ስለሰሜኑ ጦርነት ፋኖን፤ የአማራን ሚሊሺያ እና በአጠቃላይ የአማራውን ህዝብ ወንጀለኛ የሚያደርጉ መሰረተ ቢስ ዘገባና መግለጫዎች ሲያዥጎደጉዱ የፌደራሉም ሆነ የክልሉ መንግስታት ረብ ያለው ማስተካከያ ሳያቀርቡ መቅረታቸው።
ለ) ጦርነቱ ሳያልቅ፣ የተያዙ ቦታዎች ነፃ ሳይወጡ እና የህወሃት ታጣቂዎች ትጥቅ ሳይፈቱ፣ አማራና አፋር ወገኖቻችን በህወሃት ወረራ ስር በረሃብ እየረገፉ ባለበት፤ ህወሃት“የድህረ ጦርነት እቅዶች” በሚል ማደናገሪያ መንግስት ፋኖን ትጥቅ ማስፈታት ቀዳሚ ተግባሩ እንደሆነ በግልጽ በማወጅ በአማራው ህዝብ ኅልውና ላይ እያሴረ መሆኑ።
ሐ) በአማራ ህዝብ ግንባር ቀደም መስዕዋትነት ነፃነታቸውን የተቀዳጁትን የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት እና ራያ አካባቢዎች ግማሾቹን በህወሃት ተመልሰው እንዲያዙ በመፍቀድ፣ ህወሃት መልሶ ከገባቸው ቦታዎች ሳይወጣ ጦርነቱ እንዳለቀ በማወጅ፤ እንዲሁም ነጻ ለወጡት አካባቢዎች ምንም አይነት በጀት ባለመስጠት፤ አገራዊ ማዕቀብ መጣሉ እና ህዝቡን ለችግር እና መከራ መዳረጉ፤
መ) የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በህወሃት ወረራ ግዜ ጨርሶ ከመደምሰስ ያዳነውን የምስራቅ አማራ ፋኖ በማሳደድ ወልዲያ ላይ በከባድ መሳሪያ መደብደቡና ቀደም ብሎም በጎጃም እና በጎንደር ፋኖዎች በመንግሥት ኃይሎች እየታደኑ መገደላቸው፤ ይህ የአማራውን ራስን የመከላከል አቅም የማዳከም መንግስታዊ እቅድ እንደሆነ ያሳያል።
ሰ) “ሸኔ”፣ “የኦሮሞ ነፃ አውጭ ሰራዊት”፣ ”ያልታወቁ ኃይሎች” እየተባሉ በአማራ ህዝብ ላይ በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ያደርሱ የነበሩ ሃይሎች፣ በቅርቡ በምንጃርና በአካባቢው ሚሊሻዎች በተደረገው ጥቃትን የመመከት ውጊያ ከተገኙ ማስረጃዎች አጥቂዎቹ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሙሉ ድጋፍ የሚሰጣቸው መሆኑ መታወቁ፤ እነዚህ ጥቃቶች መዋቅራዊ ድጋፍ እንዳላቸው ማጋለጡ እና ይህ የአማራውን የኅልውና ስጋት በጣም አሳሳቢ እንደሚያደርገው፡
ረ) ይህ ሁሉ ሲሆን በግለሰብ ደረጃ የተደረጉ ተቃውሞዎችን ሳይጨምር በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው አማራን እንወክላለን ብለው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እንዲሁም በስሙ በጀት ወስዶ የሚያስተዳድረው ድርጅት የመረረ ተቃውሞ አለማሰማታቸው፤ በአማራው ላይ የተጋረጠበትን ከፍተኛ የኅልውና አደጋ ሁኔታውን በሚመጥን ደረጃ ህዝቡ እንዲያውቀው አለማድረጋቸው፤ ባጠቃላይ ሁኔታውን የሚመጥን የአደጋ ግዜ አመራር አለመታየቱ የአመራር ጉድለቱን አሳሳቢነት ማጋለጡ፤
ሸ) በጎንደር፤ በደባርቅ፤ በወራቤ የሃይማኖት ብጥብጥ ያለ ለማስመሰል በተሸረበ ሴራ በሙስሊምና ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥቃት እና የቤተ እምነቶችን መቃጠል እያወገዝን ፤ እንዲህ ያለው አሳፋሪ ተግባር በፊት ለፊት አማራን ለማጥፋት ከተከፈቱ ጦርነቶች በተጓዳኝ፤ እርስ በእርስ በተለያየ የክፍለሃገር፤ የሃይማኖት ወይም ሌሎች ንዑስ የባህል ልዩነቶች አማራውን እንዲሁም መላው ኢትዮጲያዊያንን መከፋፈል እንደ ዋና የጥቃት መንገድ ተደርጎ በጠላቶቻችን እንደተወሰደ ገላጭ መሆኑ።

እነዚህ ከላይ ከሀ እስከ ሸ የተጠቀሱት ነጥቦች አማራውን የማጥፋቱ እቅድ አፈጻጸሙ እየሰፋና እየጠነከረ እንደመጣ ከሚያመለክቱት ከብዙዎቹ ሰሞነኛ ኹነቶች ጥቂቶቹ ናቸው። ይህንንም በመገንዘብ፤ የአማራውን የኅልውና ትግል በተቀናጀ አኳኋን ለመምራት በየደረጃው መካሄድ ያለባቸውን ሁሉን አቀፍ ውይይቶች ከማዘጋጀት ጎን ለጎን፤ በየአቅጣጫው እየተሰነዘሩብን ያሉትንና የተደገሱልንን የተቀናጁ ጥቃቶች ለመመከት እንዲቻል የአስቸኳይ ግዜ ተግባራትን ለይተን የሚከተለውን ቁርጠኛ የጋራ አቋማችንን ለመላው የአማራ ህዝብ አቅርበናል። እነዚህ ነጥቦች መነሻ ሆነው በተለያዩ መድረኮች ውይይት እየተደረገባቸው ስማቸውን በመግለጫው ካሰፈሩ ድርጅቶች ባሻገር የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ፤ በሂደት እየተወያዩ አቋም እንዲይዙባቸው እንጋብዛለን!

1ኛ: በአሁኑ ጊዜ የአማራ ህዝብ የኅልውና ዋስትና ፋኖ ነው። የወያኔ ወረራ ለስልጣኑ ያሰጋው መንግሥት ድረስልኝ ሲለው ህይወቱን ሰጥቶ የአማራን እና የኢትዮጵያን ኅልውና የታደገው ፋኖ ነው። ስለዚህ አማራው ራሱን የሚከላከልበትን አቅም ለማሳጣት የተከፈተውን ፋኖን የማጥፋት ዘመቻ አምርሮ ከመቃወም አልፎ ባለው አቅም እና ባመነበት ሁሉ ፋኖን በማጠናከር ከየትኛውም ወገን የሚሰነዘሩ ትንኮሳዎችን እንዲመክት እናሳስባለን። ለዚህም እቅድ አውጥቶ የተለያዩ ጥቃትን የመመከት ቅደመ ዝግጅቶችን እንዲያደርግ እና ቀጣይነት ባለው አሰራር ፋኖን እንዲያጠናክር እናሳስባለን።

2ኛ፡ የአማራ ህዝብ በከፈለው ግብር የተቋቋሙ የደህንነት እና ፀጥታ ተቋማት በቀጥታ እንዲጠቃ እየተደረገ ነው። ይህን በመረዳት አማራው የደህንነቱን አደራ ለፋኖ ሰጥቶ የሚያምንበት መንግሥት እስከሚመጣ ድረስ እንደ አስፈላጊነቱ ግብር ላለመክፈል ማደም አለበት።

3ኛ አማራው እንዲለወጥለት ለሚታገለው ሥርዓት ተገዢ እንዲሆን በስሙ በጀት ተቀብለው የተሰየሙት አስተዳዳሪዎችና በስሙ ተመዝግበው አማራን እንወክላለን ብለው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ በማዕከላዊው መንግሥትና በአማራው ስም በሚጠራው ክልል ውስጥ የደረጁትን የኦሮሞ ሃይሎች ጨምሮ በኦነጋውያን ለአማራው የተደገሰለትን ጥቃት ከማውገዝና ከማጋለጥ አልፈው ስጋትና አደጋውን የሚመጥን አማራዊ አስተዋጽዖ በማድረግ በስሙ የሚምሉለትን ህዝብ ከእልቂት እንዲታደጉ እናሳስባለን።
4ኛ፡ በግንባር በሚደረገው ጦርነት ላይ የማይሳተፉ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍሎች እንደየእውቀታቸው እና ሙያቸው ለአማራው የኅልውና ትግል ድጋፍ እንዲሰጡ እናሳስባለን።
5ኛ፡ ያለንበት ወቅት በሰሜን የትህነግ ኃይሎች፤ በምዕራብ የጉሙዝ፤ እና ሌሎች ፅንፈኛ ኃይሎች፤ በደቡብ ምዕራብ በደቡብ እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በኦነግ እና በመላው ኢትዮጵያ ደግሞ በኦህዴድ ብልጽግና በኢትዮጵያ መከላከያ እና በሌሎች የፌደራል ኃይሎች በመታገዝ በአማራ ላይ የተቀናጀ ጦርነት የተከፈተበት ጊዜ በመሆኑ፤ ማንኛውንም ከኅልውና ትግሉ ውጭ ያሉ ስራዎች ለግዜው በመግታት፤ አማራ ሁሉ በኅልውና ትግሉ እና በምግብ ራስን በመቻል ላይ በማተኮር እራስን ጨርሶ ከመጥፋት ለመታደግ የሚያስችል የተቀናጀ ዘመቻ ማድረግ ይኖርበታል! ይህም ህዝቡ ያለ ሃሳብ እፎይ ብሎ የሚኖርበትን ሁኔታ የውስጥ እና የውጭ ጠላትን በማሸነፍ እስከሚያረጋገጥ መቀጠል ይኖርበታል!
6ኛ ለአማራው የታቀደለት ጥፋት በክልል የተወሰነ አይደለም። የአማራው ራስን የማዳን ትግልም በድንበር መወሰን የለበትም። የአማራ ኃይል መድረስ በሚችልባቸው ቦታዎች ሁሉ እየደረሰ የወገኑን ደህንነት የማስከበር ሙሉ መብት እንዳለው በማመን መንቀሳቀስ ይኖርበታል። ያለምንም ማመንታት እንደ መተከል፤ ደራ፤ ጠለምት፤ ራያ ባሉ አካባቢዎች በጠላት ስር የወደቁ አማሮችን ሰላም እና ደህንነት የማስከበር እቅድ አውጥቶ የወገናችንን ስቃይ ማስቆም የኅልውና ዘመቻው አካል መሆን አለበት።
7ኛ አገዛዙ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ያሰፈነው የመድሎ አስተዳደር እያከፋ መጥቷል። “ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም ይገባታል” በሚለው የኦህዴድ ብልፅግና ለዘብተኛ ጥያቄ የተጀመረው አዲስ አበባን ኦሮሚያ የማድረግ ሁሉም ኦነጋውያን የሚጋሩት ህልም የነዋሪዎቿን ደህንነት በሚያሰጋ ደረጃ በፍጥነት እየተፈጸመ ነው። ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች አብዛኛው የአማራ ማንነት ያለው ሲሆን የቀረውም ብዙሃኑ አማርኛ ተናጋሪ በኢትዮጵያዊነት እምነቱ ከአማራው የተለየ አይደለም። በአገሩ ላይ የተቀጣጠለው የአማራን ዘር የማጥፋት እቅድ በአዲስ አበባም ከእስካሁኑ በከፋ አኳኋን ተጠናክሮ ሊፈጸም እንደሚችል ስጋት አለ። ስለዚህ የአዲስ አበባ ነዋሪም ይህን ተረድቶ አማራን ለማጥፋት የተሰለፈውን ኃይል በሚመጥን አኳኋን ተደራጅቶ ራሱን ከጥፋት እንዲከላከል እናሳስባለን።

8ኛ፡ ማንኛውም ይህ ስርዓት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠንቅ ነው ብሎ ያመነ ኢትዮጵያዊ ነገድም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ሳይገድበው ይህን ኢትዮጵያን የማዳን ትግል እንዲያግዝ ጥሪ እናቀርባለን።
በውጭ የምንኖር የአማራ ስብስቦች ከሕዝባችን ጎን በመቆም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ እንዲፈጸሙ የምንሰራ መሆኑን እናረጋግጣለን! በተለይም በውጭ መሰራት ያለባቸውን እንደዲፕሎማሲ፣ የዓለም አቀፍ ግኑኝነት፣ የብዙሃን መገናኛ፣ የሀብት ማሰባሰብ ፣ በሩቅም ሆነ በአካል በመገኘት በሙያ የማገልገል፣ እንዲሁም መሰል የንቅናቄው የትግል ዘርፎችን ለመምራት ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን። ስለሆነም በውጭ የሚኖረው የአማራ ማህበረሰብ በቀጣይ ለምናደርጋቸው ማንኛውም ጥሪዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ በዚሁ አጋጣሚ እንጠይቃለን። የአማራ ህዝብ ለኅልውናው በሚያደርገው ዘረኞችን የማስወገድ ትግል የራሱን ኅልውና ከማረጋገጥ አልፎ ዳግም በዘረኞች የማትናወጥ አገር እንደሚገነባ አንጠራጠርም!

ድል ለአማራ ህዝብ!

ፋና (Federation of Amharas in North America – FANA)
ካሳ ለአማራ፣ በካናዳ የአማራ ማህበረሰብ ህብረት (Canadian Amhara Societies Alliance, CASA)
የአማራ ማኅበር በካልጋሪ (Amhara Association in Calgary )
የአማራ ኅብረተሰብ ማህበራዊ መድረክ በለንደን ኦንታሪዮ (Amhara Society Social Forum London Ontario)
ደጀን ለአማራ ህልውና (Dejen for Amhara Survival)
የአማራ ማኅበር በኤድመንተን (Amhara Association of Edmonton)
ዓለም አቀፍ የአማራ ትብብር (International Amhara Alliance (IAA))
የዐማራ ተራድዖ ድጋፍና መልሶ ማቛቛም ማህበር (Amhara Support, Relief & Rehabilitation Association (ASRRA))
የአማራ ማኅበር በኖርዌይ (Amhara Association in Norway)
የአማራ ማኅበር በኩዊንስላንድ አውስትራሊያ (Amhara Association in Queensland)

Latest from Blog

“ከለቅሶው ድንኳን እንውጣ!”

ቋሚ ስለሟች የሚያለቅሰው ለራሱ ነው። ለቅሶ ሙትን እንደማይመልስ እያወቅን የምናለቅሰው፣ እጦታችን የፈጠረብንን ስሜት ልናበርድ ነው። ሞቱ