/

የአንተኒ ብሊንከን የለየለት የትህነግ ወገንተኝነት ለምን?

7 mins read

በዚህ ሳምንት የማገር መገናኛ ሰሞነኛ ዝግጅት:

  • ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያላት ፍላጎት ምንድን ነው?
  • የባይደን አስተዳደር ከትህነግ ጋር እያሳየው ያለው የለየለት ወገንተኝነት የዩናይትድ ስቴትስን የቀጠናው ፍላጎት ለማሳካት ነው ልንል እንችላለን?
  • የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከሰሞኑ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባወጡት ትዕዛዝ መሰል መግለጫ ከእስካሁኖቹ የትህነግ ወገንተኝነት ከታየባቸው መግለጫዎቹ በባሰ አሁን ደግሞ የህገ መንግስትን ጉዳይ ይዞ መጥቷል:: አሜሪካን የሚያክል የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ‘ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ እንዳይነካ’ የሚል መግለጫ ማውጣት አንድምታው ምን ይሆን?
  • በባይደን አስተዳደር ውስጥ ለትህነግ ቅርበት ባላቸው ግለሰቦች ተፅዕኖ የወደቀው የስቴት ዲፓርትመንት አቋም ተገቢው የዲፕሎማሲ ስራ ቢሰራ ሊቀየር የሚችል ጉዳይ ነበር:: በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግስት የዲፕሎማሲ እና የህዝብ ግንኙነት ስራ ክሽፈት የስቴት ዲፓርትመንትን አቋም እዚህ እንዲደርስ አስተዋፅኦ አድርጓል:: ጉዳዩ አሁን ባለበት ሁኔታ በኢትዮጵያ መንግስት ምን አይነት የዲፕሎማሲ እና የህዝብ ግንኙነት ስራ ሊሰራ ይገባል?
  • ኢትዮጵያውያን እና ተውለደ ኢትዮጵያውያን የዳይስፖራ ማህበረሰብ አባላት የአገራቸውን የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ ምን አይነት ስራ ሊሰሩ ይገባል?• ኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁለት ጊዜ የፀጥታው ምክር ቤት ርዕስ ሆናለች:: የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ከአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እና ከተፋሰሱ አገራት ጉዳይ አልፎ ለምን ወደፀጥታው ምክር ቤት ሄደ? ከስብሰባውስ ምን ውጤት ተገኘ?
  • የባይደን አስተዳደር ከተሰናባቹ የትራምፕ አስተዳደር በተለየ ሁኔታ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ያሳየው መለሳለስ ምክንያት ምንድን ነው?በእነዚህ ርዕሰ ጉዳዯች የተወያዪት ተመስገን መንግስቱ እና ሆነ ማንደፍሮ ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ መረጃዎችን አካፍለውናል::

እኛው ነን!!

መልካም ቆይታ!!

Latest from Blog

“ከለቅሶው ድንኳን እንውጣ!”

ቋሚ ስለሟች የሚያለቅሰው ለራሱ ነው። ለቅሶ ሙትን እንደማይመልስ እያወቅን የምናለቅሰው፣ እጦታችን የፈጠረብንን ስሜት ልናበርድ ነው። ሞቱ