የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) በዩናይትድ ስቴትስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተግባር ጥሪ አቀረበ።

7 mins read

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከሰሞኑ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባወጡት ትዕዛዝ መሰል መግለጫ በመላው ዓለም የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን በተለያየ መንገድ እየገለፁ ይገኛሉ።ብዙዎችን ያስቆጣው የአንተኒ ብሊንከን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሸባሪው ትህነግ ጋር የከፈተው ጦርነት በድርድር እንዲፈታ እና ችግሩ እስኪፈታ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የህግ ለውጥ እንዳታደርግ ያስጠነቅቃል።

ይህንኑ የአንተኒ ብሊንከንን መግለጫ ለመቃወም በዩናይትድ ስቴትስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተዘጋጀው የተቃውሞ ዘመቻ ተሳታፊዎች በቀላሉ እንዲከውኑት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን የአስተባባሪው ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ ለማገር መገናኛ ገልፀዋል።

ቁጣ ብቻውን መፍትሔ አያመጣም ያሉት አቶ ቴዎድሮስ ይህ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል ማንኛውም አገር ወዳድ ቁጣውን በተግባር ሊያሳይ ይገባል ብለዋል።

በAAA የተዘጋጀው ይህ ዘመቻ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩን መግለጫ እንዲያወግዙ ይጠይቃል።

የዘመቻው መልዕክት አንተኒ ብሊንከን በተደጋጋሚ ወልቃይት፣ ሁመራ፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ዳግም በትህነግ ቁጥጥር ሥር መሆን እንዳለባቸው የሚያመላክቱና አድሏዊ መግለጫዎችን ሲያወጡ መቆየታቸውን አስታውሶ፣ በሰጧቸው መግለጫዎች ሁሉ በአማራ ክልል ሃይሎችና ሚሊሺያዎች ደረሱ ያሏቸውን ጥፋቶች በተደጋጋሚ ሲያወግዙ፣ ትህነግ በአማራው ላይ ያደረገውን ታሪካዊ ዘር የማጽዳት ጭፍጨፋና ማሳደድ አንድም ጊዜ አለመጥቀሳቸውንና ስለማይካድራው ጭፍጨፋ እንኳን አንዲት መግለጫ አለማውጣታቸውን በአጽንኦት ያመለክታል። እንዲሁም እነዚህ አስተያየቶች ለአማራው እንዲሁም በኢትዮጵያ ነገዶች መሃል ላለው ግንኙነት ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ከአገራቸው ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለምክርቤቱ ሊነግሩት ይገባል ሲል ጥሪውን ያሰማል።

የዘመቻውን መከወኛ ቅፅ ከዚህ በታች ያገኙታል።

https://amharaamerica.salsalabs.org/july2021blinkenresponse/index.html

Latest from Blog

“ከለቅሶው ድንኳን እንውጣ!”

ቋሚ ስለሟች የሚያለቅሰው ለራሱ ነው። ለቅሶ ሙትን እንደማይመልስ እያወቅን የምናለቅሰው፣ እጦታችን የፈጠረብንን ስሜት ልናበርድ ነው። ሞቱ