በውጭ አለማት የሚንቀሳቀሱ የአማራ ሲቪክ ድርጅቶች ለአማራ ህዝብ የአንድነት ጥሪ አቀረቡ
በውጭ አለማት የሚንቀሳቀሱ የአማራ ሲቪክ ድርጅቶች ለአማራ ህዝብ የአንድነት ጥሪ አቀረቡ

በሰሜን አሜሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በአውስትራልያ እና በኒውዝላድ የሚንቀሳቀሱ የአለም አቀፋ የአማራ ንቅናቄ አካል የሆኑ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ ለአማራ ህዝብ የአንድነት ጥሪ አቅርበዋል::

“ሆደ ሰፊነት፣ አስተዋይነት፣ ፍርድ አዋቂነት ታላቅ እሴቶችህ የመሆናቸውን ያህል፣ ራስን ከጥቃት እንዲሁም ዘርን ከጥፋት መከላከልም ተፈጥሯዊ መብትህ ነው”

ያለው የድርጅቶቹ የጋራ መግለጫ

“በየደረጃው የራስህን አመራር እየፈጠርህ አካባቢህን ነቅተህ ጠብቅ”

በማለት ለመላው አማራ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል::

የመግለጫውን ሙሉ ቃል እንሆ :-

ዓለም-አቀፍ የዐማራ ንቅናቄ፣ መግለጫ፣ ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ እና የሀገር የመከላከያ ሰራዊቱን ከትግራይ ማስወጣቱን ተከትሎ ትህነግ በማናቸውም ጊዜ በዐማራ ላይ ጦርነት እንደሚከፍት በዓለም—አቀፍ መገናኛ ተቋማት በይፋ አውጇል። ስለሆነም ይህንን በህዝባችን ላይ የተጎሰመ የጦርነት ነጋሪት ከፍተኛ ግምት በመስጠት በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ የሚኖረው በአጠቃላይ ዐማራው የታወጀበትን ጦርነት በአንድነት ለመመከት አስፈላጊውን እና ሁሉን አቀፍ ዝግጅት እንዲያደርግ የተሰጠ መግለጫ !

የተከበርከው የዐማራ ህዝብ ሆይ!

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዜግነት እኩል ተከብሮ እንዲኖርባት በደምህና በአጥንትህ ለዘመናት ጠብቀህ ባቆየሃት አገርህ፣ በባእዳን እና በከሃዲ ነገዳውያን ጠላቶችህ በነገድ ማንነትህ ተለይተህ “ጨቋኝ”፣ “ትምክህተኛ” “መጤ” እና “ወራሪ” የሚል የመገደያ ስያሜዎች በይፋ ተሰጥቶህ፤ ከአጽመ-ርስትህ እና ከመኖሪያ ቀየህ ስትፈናቀል፣ ስትሳደድ፣ ስትገደል፤ ወንድ ልጆችህ ከነነፍሳቸው ሲቀበሩ፤ ሴት ልጆችህ ዘር እንዳይተኩ እንዲመክኑ ሲደረጉ እና ሲደፈሩ ሃምሳ አመታት ተቆጥረዋል።

ከራስህ በላይ ለምትሳሳላት ኢትዮጵያ ብለህ ተነግሮ የማያልቅ ግፍ/መከራ ችለህ አሳልፈሃል። አንተ ብትተዋቸው የማይተውህ፤ መጥፋትህን የሚመኙ ጠላቶችህ ከመቸውም ጊዜ በላይ እንቅልፍ አጥተው፣ ተቀናጅተው እና ተማምለው ተነስተውብሃል።ሆደ ሰፊነት፣ አስተዋይነት፣ ፍርድ አዋቂነት ታላቅ እሴቶችህ የመሆናቸውን ያህል፣ ራስን ከጥቃት እንዲሁም ዘርን ከጥፋት መከላከልም ተፈጥሯዊ መብትህ ነው። ይህን ወቅቱ ያመጣብህን ጥቃት እና አደጋ ስፋት እና ጥልቀቱን ተገንዝበህ ልክ እንደ አባቶችህ “ተቻችለህ” በዐማራነትህ በአንድ ላይ የምትቆምበት፣ የምትደጋገፍበት፣ አንድህ ለሌላው ተገን እና አለኝታ የምትሆንበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነህ። የጠላቶችህ ዋናው ሴራ አንተ አንድ ሆነህ እንዳትቆም በመሃልህ ገብተው መከፋፈል ነው። ምክንያቱም አንተ ስትተባባር እንኳን ለራስህ ለሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖችህ አለኝታ እና መከታም መሆንህን ጠንቅቀው ያውቁታልና።

እናም በየደረጃው የራስህን አመራር እየፈጠርክ አካባቢህን ነቅተህ ጠብቅ! እራስህን እና ሕዝብን ልታድን እና ድንበርህን ልታስጠብቅ የምትችለው ተባብረህ ስትቆም ብቻ ነው። ከያለንበት ባንድ ሃሳብ፤ አንድ ልቦና እና ዓላማ የማንሻገረው የታሪክ አቀበት አይኖርም! በየአቅጣጫው ጦር የሰበቁብንም ሃይሎች ታሪክ አድርገን በድል ህልውናችንን እናስጠብቃለን! ከሀገር ውጭ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ መሬት ላይ ካሉ ወገኖቻችን ጋር በመነጋገር ቀጣይ ስራዎችን የምናሳውቅ ይሆናል!

የአባቶቻችን ልጆች ነን!

አንድ ዐማራ!

  • ፋና (Federation of Amharas in North America – FANA)
  • ካሳ ለአማራ፣ በካናዳ የአማራ ማህበረሰብ ህብረት (Canadian Amhara Societies Alliance, CASA)
  • ደጀን-የአማራ ማህበራት መድረክ በአውሮፓ (ደ-አማራ – DEJEN)
  • የዐማራ ማህበራት ሸንጎ በአውስትራሊያ (Amhara Associations Council in Australia – AACA)
  • የዐማራ ተርድዖ ድጋፍና መልሶ ማቛቛም ማህበር (ASRRA)
  • ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

Latest from Blog

“ከለቅሶው ድንኳን እንውጣ!”

ቋሚ ስለሟች የሚያለቅሰው ለራሱ ነው። ለቅሶ ሙትን እንደማይመልስ እያወቅን የምናለቅሰው፣ እጦታችን የፈጠረብንን ስሜት ልናበርድ ነው። ሞቱ