ጌታቸው በየነ በዚህ ሳምንት የማገር እንግዳ ዝግጅቱ ወጣቷን ጸሐፊ እና መምህርት መስከረም አበራ ይዞልን ቀርቧል:: የውይይታቸው ትኩረት መስከረም ከሰሞኑ “የአማራ ህዝብ ትግል ዳራ እና የትግል አቅጣጫዎች” በሚል ርዕስ ለህዝብ ባሰራጨችው ሰንድ ዙሪያ ነው:: ጌታቸው “መስከረም አበራ በአማራው ንቅናቄ ድርሻዋ ምንድን ነው” በማለት ጥያቄውን ይጀምራል:: ከተነሱት በርካታ ነጥቦች መካከል ትቂቶቹ: “አገራዊ ምክክር”ን አስመልክቶ 1. ኮሚሽኑ የሚያቀርባቸው ዋና ዋና መገጋገሪያ ጉዳዮች ምን ይሆናሉ? 2. ዋናዎቹ የልዩነት መሠረት የሚሆኑት ጉዳዮች ምንድን ናቸው? 3. በስልጣን ላይ ያለውን ጨምሮ በአገሪቱ ፖለቲካ ጎላ ብለው የሚታዩና የሚታወቁት ድርጅቶች አሰላለፋቸው እንዴት ይሆናል? 4. የአማራው የምንለውን አስተሳሰብ ደግፈው የሚቆሙ ቡድኖችን ማሰብ ይቻላል? 5. የአማራው አስተሳሰብ በማን ሊወከል ይችላል? የአማራን ህዝብ ወክሎ ለድርድር የሚቀርበው ማን ነው? ህዝቡን ለመወከል አንድ ቡድን ወይም ግለሰብ ምን ምን ማሟላት ይገባዋል? ህዝብን እወክላለሁ ሲባል መሟላት ያለባቸው ጉዳዯች ምን ምን ናቸው? 6. ብአዴን የአማራ ወኪል ሆኖ መቅረቡ ምን ሊያስከትል ይችላል? 7. የልዩነት መሠረት ካልናቸው ሃሳቦች አንጻር አማራው ጠንካራ አቋም የሚይዝባቸው የትኞቹ ይሆናሉ? 8. መንግሥትን ጨምሮ በብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚወከለውን ኦነጋዊ አስተሳሰብ አማራው እንዴት ሊረታ ይችላል?
Latest from Blog
በዛሬው የቅድሜ ሰሞነኛ ዝግጅታችን የምናነሳው የፋኖ ጉዳይ ሰፊ ርዕስ በመሆኑ በቀጣይ ዝግጅቶቻችን ሰፋ አድርገን እንመለስበታለን:: ለዛሬ
የአማራ ህዝብ ያለበትን የኅልውና ስጋት በማገናዘብ ኅልውናውን ለማስከበር መወሰድ ስለሚገባቸው ቆራጥ እርምጃዎች ከዓለም አቀፍ የአማራ ማኅበራት የተሰጠ መግለጫ።
ሚያዚያ 20 ቀን 2014 ( አፕሪል 29 2022)| በቃን! የመጨረሻው ሞገድበሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአማራ ማኅበራት መሪዎች
በወለጋ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች የድረሱልን ጥሪ፣በራያ ቆቦ አዲስ የጸጥታ መመሪያ ተላለፈ፣ሱዳን አልፋሽጋ ግዛቴ ነዉ እወቁልኝ አለች
በወለንጭቲ ከባድ ተኩስ ተከፍቷልየሸዋሮቢቱ ጥቃት ሰለባዎችየሩሲያ ኢምባሲ ማስተባበያኮሎኔል ደመቀ ምን አሉ?