አገር ከማጣት ስጋት የገቡበትን ጠብ ትጥቅን አጥብቀው እንጂ ተሸማግለው አይወጡትም!

18 mins read

‘ከክልላቸው ውጭ ይኖራሉ’ ያላቸውን ወገኖቹን ፈጅቶና አስሰድዶ ደጀኑን ሕዝብ አለተከላካይ ለእልቂት ሊያጋልጠው እደጁ ከደረሰው ፀረ-አማራ ኃይል ጋር የሞት-ሽረት ጦርነት የገጠመውን የአማራ አርበኛ ‘በሽምግልና ሰበብ ትጥቁን እያስፈቱት ነው’ የሚል ወሬ ይስሰማል። ይህ እውነት ከሆነ፣ ትጥቁን ለሚፈታው የአማራ አርበኛ የረሳውን የሽምግልና ባህሉን ማስታወስ ያስፈልጋል።

ሽምግልና በግለሰቦች መካከል፣ በቤተሰብና በቤተዘመድ ውስጥ፣ ከፍ ሲልም በማኅበረሰባዊ ቡድኖች መካከል የሚከሰቱ ቅራኔዎችና ግጭቶች ማኅበራዊ ሕይወትን እንዳያውኩ፣ በጠበኞቹ መሃል በኃላፊነት መንፈስ ሽማግሌዎች ጣልቃ እየገቡ የጠብ ምክንያት የሆኑ ተቃራኒ ፍላጎቶችን በማቻቻል ጠብን የሚያስወግዱበት የኑሮ ብልሃት ነው።

ለዚህ ኃላፊነት የሚበቁ ሽማግሌዎች፣ በትምህርትም ሆነ በሕይወት ተመክሯቸው እውቀትን ያካበቱ፤ በማኅበረሰብ ተቆርቋሪነታቸው፣ በአስተዋይነታቸው፣ በመካሪነታቸው፣ በፍትሕ አዋቂነታቸውና በቆራጥነታቸው በማኅበረሰቡ አባላት ዘንድ ተሰሚነትና ክብር ያገኙ፤ የወገናቸውን ማኅበረሰባዊ ኅሊና የሚወክሉ ኅሩያን ናቸው።

አሁን በአማራው ክልል ያለው ግጭት፣ የነገዳዊው ሕገመንግሥት አስፈጻሚ የሆነው ኦነጋዊ ቡድን በሚመራው የመንግሥት ሠራዊት እና ይህ ሕገመንግሥት የህልውና አደጋ ባስከተለበት ሕዝብ መካከል የሚደረግ ጦርነት ነው። ለመሆኑ በኦነጋዊው መንግሥትና ጦርነት በታወጀበት የአማራ ሕዝብ መሃል “አንተም ተው፤ አንተም ተው” ብለው የሚገቡ፣ በሁለቱም ወገኖች የታፈሩና የተከበሩ ሽማግሌዎች ዛሬ ከወዴት ተገኙ?

አማራ ንቃ! እነዚህ የአብይ አሕመድ ምንደኞች የሚያካሂዱት ሽምግልና አይደለም። መርዝም በምግብና በመጠጥ ነው ተሰውሮ እሚቀርብ፤ ለአማራ ኅልውና በግንባር ቀደምነት የሚፋለመው ፋኖም ሆነ ደጀኑ ሕዝብ በነገዳውያኑ ዘመን በፈሉት ሽማግሌ መሳይ ደላላዎች እየታለለ ውድቀቱን እንዳያፋጥን በወያኔ ዘመን በ”ቅንጅት” ስም በተነሳው ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ላይ፣ ዛሬም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ በቆረጡ አባቶችና ምእመናን ላይ በሽምግልና ስም ከተሰራው ሸፍጥ ሊመከር ይግገባዋል።

ሽማግሌዎች ጠበኞችን የራስ አድርገው የሚመለከቱና ስለእውነት ሁሉንም ወገን የሚያሸንፉ/የሚረቱ ናቸው። ግን፣ አማራን አገር አልባ ሊያደርግና ሊያጠፋ፣ በመቃብሩም “ኦሮሞነትን” ሊያንጽ የተነሳው ኦነጋዊው የአብይ አሕመድ መንግሥት ለአማራው የራስ መንግሥት ነው እንዴ?

ሽማግሌዎች እኮ፣ የራሳቸውን ጠበኞች ያስታርቃሉ እንጂ በገዛ ጠባቸው ገላጋይ አይሆኑም። በገዛ ጠባቸውማ፣ ብርቱዎቹ ከፊት እየቀደሙ የሚፋለሙና የሚመሩ፣ አረጋውያኑ ተፋላሚውን የሚያበረቱ ደጀኑን የሚያተጉ ናቸው። የአብይ አሕመድ ‘ሽማግሌዎች’ ከአማራው መሃል የወጡ ቢሆኑም ከብአዴን ጎራ የተሰለፉ የአማራው መቅሰፍቶች እንጂ የወገን መድኅን አይደሉም!

በሽምግልና ስም ለአብይ አሕመድ ኦነጋዊ መንግሥት አገልግሎት የሚሰጡ ብአዴናውያን ደላላዎች ቁርጠኛ የአማራ አርበኞችን ለማጥፋት አደራ ከተቀበሉት የብአዴን ሹማምንት ተለይተው አይታዩም። እነዚህ ደላላዎች የአማራ ሽማግሌዎች ቢሆኑ ኖሮ፣ ከአማራ የተወለዱትን ከሃዲ የብአዴን ሹማምንት፣ በመጀመሪያ የተለጎሙበትን ‘ብአዴን/አዴፓ/የአማራ ብልጽግና’ የሚባል ልጓም በጣጥሰው እንዲጥሉ፣ የያዙትን የአስተዳደር መዋቅር ለቆራጥ አማራዎች አንዲያስረክቡና፣ በአማራው ላይ እስከአሁን ላደረሱት በደል ይቅርታ ጠይቀው ዘወር እንዲሉ፣ ቁጭት ያለባቸው ከተገኙም የሚያውቁትን የአማራ ጠላቶችን ሴራ በማጋለጥና በመጋፈጥ ሲበድሉት የኖሩትን ሕዝብ እንዲክሱ መምከር ነበረባቸው።

ይህ በአብይ አሕመድ ኦነጋዊ ሠራዊት በአማራው ላይ የተከፈተ ጦርነት፣ አማራው ዘላቂ ህልውናውንና ባለአገርነቱን የሚያረጋግጥበት መራራ የአርበኝነት ትግል ጅማሬ እንጂ፣ ትርፍና ኪሳራ አስልቶ ለእፎይታ የሚደራደሩበት የመጨረሻ ምዕራፍ አይደለም። ዛሬ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የአማራ አርበኞችን መስዋዕትነት በኅሊናችን ይዘን፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በእስር የሚማቅቁ ፋኖዎቻችንን አስፈትተን ትግላችንን የምናጠናክርበት እንጂ፣ ዱር ቤቴ ያሉ አርበኞቻችንን በሽምግልና ስም እያደናገርን ለጠላቶቻችን እጅ የምንነሳበት ጊዜ አይደለም!

ተደጋግሞ እንደተገለጸው፣ አብይ አሕመድ ጦሩን ወደአማራ ያዘመተበት ዓላማ በአማራ ተወላጅ እጅ የጦር መሣሪያ እንዳይኖር ለማረጋገጥ ነው። ‘ኢመደበኛ አደረጃጀትን ማስወገድ’ ብሎ የጀመረውን ፋኖን የማጥፋት ዘመቻ፣ ልዩ ኃይሉን ወደመበተን አሸጋግሮ ክልሉን የጦር አውድማ ካደረገው በኋላ በ“ሽምግልና” ስም ተዋጊውን ኃይል ለማዘናጋት ከሚያደርገው ጥረት አልፎ፣ ገበሬው ለንብረቱ መጠበቂያ የገዛውን ማሣሪያ ለመግፈፍ “ትጥቃችሁን ካላስረከባችሁ ማዳበሪያ አታገኙም” የሚል የውንብድና እና የአፈና ዘዴ እየተከተለ እንደሆነ ይስሰማል። ይህ ሁሉ ዘመቻ ተሳክቶለት አብይ አሕመድ አማራውን ትጥቅ ካስፈታ በሕይወት የሚተርፍ አማራ የሚቆየው ለባርነት ኑሮ መሆኑን ሊገነዘበው ይግገባል!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“ከለቅሶው ድንኳን እንውጣ!”

ቋሚ ስለሟች የሚያለቅሰው ለራሱ ነው። ለቅሶ ሙትን እንደማይመልስ እያወቅን የምናለቅሰው፣ እጦታችን የፈጠረብንን ስሜት ልናበርድ ነው። ሞቱ